2B+G+13
2B+G+13
ቤት፣ ቤት ለሌላቸው!!!
ዓላማችን የከተማችንን የቤት ችግር ማቃለል ነው
ባለ 13 ወለል ሕንፃ
ዓላማችን የከተማችንን የቤት ችግር ማቃለል ነው
ባለ 13 ወለል ሕንፃ
ኑ!!! ቤታችንን በጋራ እንገንባ
ባለ 13 ወለል ሕንፃ
ኑ!!! ቤታችንን በጋራ እንገንባ
❮
❯
አዳዲስ መረጃዎች
የሀላፊ ስም ፡- መስከረም ዘውዴ ፈለቀ(ዶ/ር)
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮም በከተማዋ የሚታዩትን የመኖሪያ ቤት ችሮችን ለመፍታት ትልቅ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም ነው፡፡ ቢሮው ሀገር አቀፍ ፖሊሲዎችንና የህግ ማዕቀፎችን መሰረት በማድረግ የተለያዩ የቤት አማራጮችን አቀናጅቶ በመምራት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ጥራት ያለውና ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የመክፈል አቅም ያገናዘበ አሳታፊ የመኖሪያ ቤት እንዲገነባ በማድረግ የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ባለቤት ለማድረግ ኃላፊነት ወስዶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የከተማዋን ልማት በማፋጠን፣ የስራ እድል በመፍጠር፣ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እውቀት ሽግግር በማድረግ፣ የህብረተሰቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና በከተማ አስተዳደሩ በባለቤትነት የተያዙ የመኖርያና ንግድ ቤቶችን የማስተዳደር ኃላፊነት ወስዶ እየሰራም ነው፡፡
ራእይ
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች አቅም ያገናዘበ ጥራት ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች እንዲቀርቡ በማድረግ በ2017 ዓ.ም የቤት ባለቤት ሆነው ማየት፡፡
ተልእኮ
• በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለማሳካት የሀገር አቀፍ ፖሊሲዎች ፣ የህግ ማዕቀፎች ስታንዳርዶችና ስልቶች መሠረት የተለያዬ የቤት አማራጮችን መንግስት ከሚያለማው ጋር አቀናጅቶ ለመምራት የሚያስችል የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ወጪ ቆጣቢ ጥራት ያለውና የቤት ፈላጊውን ህብረተሰብ የመክፈል አቅም ያገናዘበ አሳታፊ የመኖሪያ ቤት እንዲገነባ በማድረግ የከተማውን ነዋሪ የቤት ባለቤት ማድረግ፡፡