የ2018 በጀት ዓመት የKPI እቅድ ላይ ቢሮው...

image description
image description
- ውስጥ ወቅታዊ ጉዳዮች    0

የ2018 በጀት ዓመት የKPI እቅድ ላይ ቢሮው ከኮርፖሬሽኑ እና ከዘርፎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ

 

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ2018 በጀት አመት KPI እቅድ ላይ ከቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና ከዘርፎች እንዲሁም ዘርፎች ከዳይሬክቶሬቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ተፈራረሙ ።

በበጀት ዓመቱ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ የሆነውን ቤት ገንብቶ የማስተላለፍ እቅድ ለማሳካት ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ ከምንግዜውም በላይ በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል በማለት የቢሮ ኃላፊዋ ክብርት ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት ገልፀዋል፡፡

የስምምነት ፊርማውም በ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና ግቦች ላይ በመግባባት ስራን ቆጥሮ ስጥቶ ቆጥሮ ለመረከብ እና አፈፃፁሙን እየገመገሙ ለመሄድ  ያግዛል ብለዋል፡፡

እቅዶቻችንን ለማሳካትም የሁሉቱ ተቋማት አመራሮች እና ስራተኞች ከተለመደው የመደበኛ የስራ ስእት ውጪ ለመስራት ዝግጁ መሆን ይገባቸዋል በማለት ኃላፊዋ አሳስበዋል፡፡

በፊርማ ስነስርዓቱም የ2018 በጀት ዓመት የKPI እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡


በቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.